ኤክቱስ ጥር 4/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ማረሚያ ተቋም በሚገኘው በወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ አስራ አንድ የሕግ ታራሚዎች በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።
ተጠማቂዎቹ ከዚህ በፊት የቅድመ ጥምቀት መደበኛ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውንና አሁን ደግሞ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ነገረ ኃይማኖት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን እና ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እየተማሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በተጨማሪም የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌልና የምግባረ ሰናይ ክፍላት ከመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት እንዲሁም ከማረሚያ ቤቱ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር በመተባበር እንደተሠራና ሌሎችም በርካታ ሥራዎች በመሠራት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ተጠማቂያኑ በኃይማኖት እንዲጸኑና እንዲበረቱ እንዲሁም መንፈሳዊ ትምህርታቸው በሚገባ እንዲከታተሉ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰው በጸሎት ፈጽመዋል።
