ኤክቱስ ኅዳር 13/2018 ዓ.ም
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራሮችና ከዲላ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
ውይይቱ ትኩረቱን ያደረገው ሀገረ ስብከቱ ከማኅበሩ ጋር በጋራ ለመሥራት በተፈራረመው ውል ላይ ሲሆን በቀጣይ ከማኅበሩ ጋር በጋራ ለመሥራት ባሰባቸው ሥራዎች ላይ ግልጽ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋስይሁን፣ የማኅበሩ ደቡብ ማስተባበርያ ኃላፊ ቀሲስ አሰፋ ቦረና፣ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከልና ዲላ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚዎች ተሳትፈዋል።
