በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቆቲ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኘው በቆቲ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

መርሐ ግብሩን የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ ሊቀኀሩያን እሸቱ ዋለ የመሩት ሲሆን ትምህርተ ወንጌል የሰጡትና ለቤተክርስቲያን የልማት ሥራ ያስተባበሩት የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ ሲሆኑ በትምህርታቸውም ሩፋኤል ማለት እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ማለት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ሩፋኤል ማለት ፈታሄ ማኅፀን ማለት ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ጸሎት ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል ።

Scroll to Top