በጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስ ዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ፣ የወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀጠበብት መሪጌታ መሠረት እና ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን እሸቱ ዋለ ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል መሪጌታ ሀብቴ ፣የየአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ሊቀውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተገኙ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከብሯል ።
#በዕለቱም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለድቁና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ44 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ድቁና የሰጡ ሲሆን ለቅስና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ10ት ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጥተዋል።
#ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ካደረገ በኋላ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል።
#በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር የዲላ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን ደምሴ በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት የመልካም ምኞትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በክብር እንግድነት የተገኙትን የዲላ ከተማ ከንቲባንና የሥራ ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል።
የዕለቱን ትምህርት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዓሉን የተ92መለከተ ስለ ቅዱሳን መላእክት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል በመላእክትና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት መነሻ በማድረግ የመላእክት እርዳታ አስፈላጊነት ገልጸዋል። የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ቅዱስ ገብርኤል እንደረዳቸውን በሰፊው ትምህርት ሰጥተዋል። በመጨረሻም ጸሎት በመድረግ የበዓሉ ፍጻሜ ሲሆን ጸሎተ ቅዳሴው በብፁዓን አባቶች ተመርቷል።





