በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የቅዱሳት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት የማይሰጡ አብያተክርስቲያናት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ለማድረግ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል ።ከዚህም በንዋየ ቅድሳት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛል ።

ከእነዚህም የቅዱሳት መጽሐፍት እጥረቱ ላለባቸው አብያተክርስቲያናት የሚሆን መጽሐፍትን መ/ርት አልማዝ ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ለሀገረ ስብከቱ ጳጳስ አስረክበዋል። ብፁዕነታቸውም ስለተሰጠው ስጦታ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም አብያተክርስቲያናቱ ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሁሉም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች የአቅማቸውን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል። ንዋየቅዱሳት ፣ ቅዱስት መጽሐፍትን ፣ልብሰ ተክህኖ አልባሳትን የካህናት ደመወዝን በመቻል የተዘጉ አብያተክርስቲያናት ማስፈከትና በረከት መቀበል አለብን እያልን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Scroll to Top