በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በወናጎ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ሰኔ ፴ ቀን በታላቅ መንፈሳዊ ክብር የሚከበረው ዓመታዊ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የልደት በዓል በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ ሊቀኅሩያን ቀሲስ እሸቱ ዋለ የወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያምና ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ግሩም በቀለ ሊቃውንት ካህናትና የወናጎና የአካባቢው ምዕመናን በተገኙበት በወናጎ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተከብረ።

መርሃግብሩ በደብሩ ዋና ጸሐፊ በሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምሕረቴ ገብረ ሥላሴ የተመራ ሲሆን ለዕለቱ የሚስማማ ወረብ በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ቀርቧል።

ትምህርተ ወንጌል የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን እሸቱ ዋለ የሰጡ ሲሆን በዕድሳት ላይ ለሚገኘው ለደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ በሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ ተሰጥቶ መርሃግብሩ በጸሎት ተፈጽሟል።

ኤክቱስ ሰኔ 30/2017

Scroll to Top