በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ።
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በመዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጽንሰት በማስመልከት የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ተጠናቋል።
በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሪጌታ መሰረት ይልማ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ሰናይ፣ ሰባኪያነ ወንጌል እና ዘማሪያን፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት፣ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
በጉባኤው የበገና ዝማሬ፣ ትምህርተ ወንጌል በተጋባዥ መምህራን፣ ዝማሬ የተሰጠ ሲሆን ጉባኤው ዛሬም እንደሚቀጥል ተገልጾ የመርሃግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።





