በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የዲላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ለጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የምስጋናና የእውቅና ምስክር ወረቀት አበረከተ!

ኤክቱስ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

የዲላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ጊዜያት ለተቋሙ ላደረገው የቁሳቁስ ድጋፍና ለሰጠው ሃይማኖታዊ አገልግሎት እውቅና በመስጠት የምስጋናና የምስክር ወረቀት አበረከተ።

የተዘጋጀውን የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከተቋሙ አዛዥ ከኢንስፔክተር ትእግስት ሮቤ ተረክበዋል።

በስነ ሥርዓቱ ወቅት ተቋሙ ሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብና ሃይማኖታዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ይህ አዎንታዊና ድጋፍ ሰጪ አጋርነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ የቀረበበት መልእክት ተካቷል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የምስጋና ምስክር ወረቀቱን ከተረከቡ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊና የማኅበራዊ አገልግሎት ተደራሽነቷን በማስፋፋት በማረሚያ ቤት የሚገኙ ወገኖች በሥነ-ምግባር ታንጸውና ተስፋ ሰንቀው ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የምታደርገውን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

Scroll to Top