በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

መልአከ ሰላም ድረስ ታደሰ የዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተመደቡ!

ኤክቱስ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ መልአከ ሰላም ድረስ ታደሰ የዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተመድበዋል።

በዕለቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴ እና ቅዳሴ ከተተረጎመ በኋላ ጸሎተ ወንጌል የተነበበ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የዕለቱን ወንጌል አስተምረው ደብዳቤውን አንብበዋል።

ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር፣ የልማት ሥራዎችን በማስፋፋት፣ ማኅበረ ካህናትንና ምዕመናንን በፍቅር በአንድነት መምራት እንደሚገባ እንዲሁም ምዕመናን ከአዲሱ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን በአንድነት ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመቀጠል አዲሱ የደብሩ አስተዳዳሪ ትውውቅ አድርገዋል።

በዕለቱ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሠረት ይልማ፣ የደብሩ ካህናትና መምህራን፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር አካላት እንዲሁም ምዕመናን ተገኝተዋል።

Scroll to Top