ኤክቱስ ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 6ተኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት አደራሽ አካሂዷል ።
በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የወረዳ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤቱ አጠቃላይ ሪፓርተር እና የየአድባራቱ የሥራ ክንውን ሪፓርት የቀርበ ሲሆን በቀረበው ሪፓርት ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በጉባኤው የተነሱ ጠንካራ የሥራ ተሞክሮዎችን አድባራት በመውሰድ የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባ እንዲሁም መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮችን በትኩረት ተመልክቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሠረት ይልማ በመርሃግብሩ ላይ ተናግረዋል።
በጉባኤው የሀገረስብከቱ ዋና ሥራአስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን እሸቱ ዋለ፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አካላትና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
