በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

መልአከ ምሕረት አባ ሀብተ ማርያም ታደሰ (ቆሞስ) የይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተመደቡ!

ኤክቱስ ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ መልአከ ምሕረት አባ ሀብተ ማርያም ታደሰ (ቆሞስ) በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት የይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተመድበዋል።

በዕለቱ የትውውቅ መርሃግብር የተደረገ ሲሆን መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ ደብዳቤውን ያነበቡ ሲሆን ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር፣ የልማት ሥራዎችን በማስፋፋት፣ ማኅበረ ካህናትንና ምዕመናንን በፍቅር በአንድነት መምራት እንደሚገባ እንዲሁም ምዕመናን ከአዲሱ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን በአንድነት ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዕለቱን ትምህርት አዲሱ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት አባ ሀብተ ማርያም ታደሰ (ቆሞስ) አስተምረው ትውውቅ አድርገዋል።

በዕለቱ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፥ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ኃይማኖት ብዙአየሁ ዳመነ፣ የደብሩ ካህናትና መምህራን፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር አካላት እንዲሁም ምዕመናን ተገኝተዋል።

Scroll to Top