ኤክቱስ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በገደብ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እየተከበረ በሚገኘው በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የእረፍት በዓል በታቦቱ ፊት በብፁዕነታቸው መሪነት የምሕላ ጸሎት ተካሂዷል።
ይህ የጸሎተ ምሕላ ሥነ ሥርዓት በሀገሪቱ ከተከሰተው የአየር ንብረት መዛባት ጋር ተያይዞ እግዚአብሔር አምላክ በቅዱሳኑ ጸሎት ምሕረቱን እንዲልክና በወቅቱ ዝናቡን እንዲያዝንም ተማጽነዋል።
