“ይቤዙ እግዚአብሔር ነፍሰ አግብርቲሁ ወኢይኔስሑ ኩሎሙ እለ ይትዌከሉ ቦቱ – የባርያዎቹን ነፍስ እግዚአብሔር ይቤዣል በርሱም የሚያምኑ ሁሉ አይጸጸቱም”
መዝ 33፥22
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሥር በሚገኘው አረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም በሕንጻ ግንባታ ምክንያት ለፊኒሽንግ ሥራ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ እስካሁን በሚያሳዝን ሁኔታ በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ሕይወታቸው ማለፉን ከሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ስንሰማ እጅግ ከልባችን አዝነናል።
ለሞቱት ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላካችን ሀገረ ሕይወትን መንግስተ ሰማያትን እንዲያወርስልን ከቅዱሳን ማኅበር እንዲደምርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲልክን ጸሎታችን ነው።
እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ!
አባ ገሪማ
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
መስከረም 21/2018 ዓ.ም