በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ በሲባ ቀበሌ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ!

ኤክቱስ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በቡሌና ራጴ ወረዳ ቤተ ክህነት በአዋሬ ጉባቶ በሲባ ቀበሌ የሚገኙ ምዕመናን ከዚህ ቀደም በአቅራቢያቸው ቤተ ክርስቲያን ባለመኖሩ ምክንያት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት ሳያገኙ ለረዥም ዘመናትና ለብዙ ወራት በመቆየታቸው ምክንያት አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በዕለቱ የጌዴኦ ብሔር የባህል ሽማግሌዎች ምርቃት ያቀረቡ ሲሆን በአከባቢው የሚገኙ ምዕመናን ደግሞ በአቅራቢያቸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሊገነባ በመሆኑ እና በዛሬው ዕለት በብፁዕነታቸው በመጎብኘታቸው እና በመባረካቸው የተሰማቸው ልዩ ደስታ ገልጸዋል።

በመቀጠል የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር አከናውነዋል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በአማርኛ፣ በጌዴኡፋ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን ቀጥለውም በመርሃግብሩ የተነበበውን የወንጌል ክፍል “አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ክብርት ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም” በሚል ርእስ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምንነት በሰፊው አስተምረዋል።

ቀጥለውም አዲስ ለሚገነባው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕነታቸው ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን እያስተባበሩ በሚያስፈልገው ከጎናቸው እንደሚቆሙ ቃል ገብተው በጸሎት ፈጽመዋል።

Scroll to Top