በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በግንባታ ላይ የሚገኘው የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ጉብኝት ተደረገ!!

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሀገረ ስብከት አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ ሀገረ ስብከቱ በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚያስገነባውን የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ጉብኝት አደረጉ።

በጉብኝቱ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች እና ጸሐፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች በጠቅላላ ጉባኤው የተገኙ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በጉብኝት ስለሕንጻው አሁናዊ ሁኔታ ገለጻ የሰጡት ኢንጅነር አማኑኤል ሲሆኑ ሕንጻው በደረሰበት ደረጃ መደነቃቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

በተጨማሪ በቅጥር ግቢ ውስጥ እየተሰሩ የሚገኙት የግብርና የልማት ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ወደፊት ስለሚሰሩ ሥራዎች ገለጻ አድርገው እንዲሁም ለመጎብኘት ለመጡት እንግዶች ምስጋና አቅርበው ፍጻሜ ሆኗል።

Scroll to Top