በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በሀገረ ስብከቱ የተለያዩ የግብርና ፕሮጀክቶችን መሥራት የሚስችል ጉብኝትና ውይይት ተደረገ!!

ኤክቱስ ኅዳር 2018 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በላዕከ ወንጌል ያሬድ አደመ አስተባባሪነት ከ”ICIPE (INTERNATIONAL CENTRE OF INSECT PHYSIOLOGY AND ECOLOGY)” ከተባለ በንብ ማነብ፣ በሐር ትል፣ እና በታዳሽ ኃይል ዙርያ ከሚሰራ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር ሊሠሩ በታሰቡ የግብርና ፕሮጀክቶች ዙርያ ውይይት እና ፕሮጀክቱ በሚሠራባቸው ቦታዎች ጉብኝት ተደርጓል።

ጉብኝቱ መነሻውን ያደረገው በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ በአንዲዳ መድኃኔዓለም የሚገኘው የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት፣ የዳማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እና በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ እየተሠራ በሚገኘው የዶሮ እርባታ ሥፍራ፣ የንብ ማነብ ሥራ እንዲሁም የሚሠሩ በርካታ የግብርና ሥራዎች ጉብኝትና ወደፊት በሚሠሩ ሥራዎች ዙርያ ጥናት ተደርጓል።

ጉብኝቱ የድርጅቱ ሠራተኞች ከሆኑት ከዶክተር ወርቅነህ አያሌው እና አቶ ልዑል ሰገድ በላይይሁን እንዲሁም ከደቡብ አስተባባሪ ዲያቆን አሳሳኸኝ ጋር ተደርጓል።

በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጽሕፈት ቤት ስለአጠቃላይ ሥራዎችና ወደፊት በምን አይነት መንገድ በጋራ መሥራት እንደሚቻል ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዕለቱ በአራቱም ቦታዎች የነበረው ጉብኝት እንዲሁም ወደፊት ሊሠሩ ስለታሰቡ ሥራዎች የተደረገው ውይይት ውጤታማ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ከዚህም በኋላ ሀገረ ስብከቱ ከድርጅቱ ጋር በጋራ ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸው እንዲሁም ይህንን ሥራ በጋራ ለመሥራት ለመጡት ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበው በጸሎት ፈጽመዋል።

Scroll to Top