በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ ሙላት ግዛው የዲላ ዳግማዊት ጌቴሴማኒ በአታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተመደቡ!

ኤክቱስ ሐምሌ 5/2018 ዓ.ም

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ ሙላት ግዛው በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት የዲላ ዳግማዊት ጌቴሴማኒ በአታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተመድበዋል።

በዕለቱ የትውውቅ መርሃግብር የተደረገ ሲሆን መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ ደብዳቤውን ያነበቡ ሲሆን ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር፣ የልማት ሥራዎችን በማስፋፋት፣ ማኅበረ ካህናትንና ምዕመናንን በፍቅር በአንድነት መምራት እንደሚገባ እንዲሁም ምዕመናን ከአዲሱ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን በአንድነት ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዕለቱን ትምህርት አዲሱ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ ሙላት ግዛው አስተምረው ትውውቅ አድርገዋል።

በዕለቱ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን እሸቱ ዋለ፣ የደብሩ ካህናትና መምህራን፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር አካላት እንዲሁም ምዕመናን ተገኝተዋል።

Scroll to Top