ኤክቱስ ሐምሌ 5/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ በንዋየ ቅድሳት እጥረት ምክንያት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት ለማይሰጥባቸው የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ፤ አረጋዊው ርእሰ ደብር ቀሲስ ለገሰ በለጠ ወልደ ሚካኤል፣ ወልደ ገብርኤል፣ ፍቅረ አማኑኤል፣ ኃይለ ማርያም፣ ኃይለ ገብርኤል እና ወልደ አረጋዊ የተባሉ መንፈሳዊ ልጆቻቸውን በማስተባበር የሁለት ሰሞነኛ ሙሉ ልብሰ ተክኅኖ፣ ሀዲስ ኪዳን፣ ተአምረ ማርያም፣ መዝገበ ቅዳሴ ከነምልክቱ (በጉልህ) እና መጽሐፈ ግጻዌ ራሳቸው አስደጉሰው ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተረከቡ ሲሆን ድጋፍ ላደረጉት አካላት ምስጋና አቅርበው ሌሎችም ምዕመናን በዚህ ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
