በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምህረቴ ገ/ሥላሴ የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዲሆኑ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተሹመዋል።

በዕለቱም የማስተዋወቅ መርሐ ግብሩን ያከናወኑት የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በሆኑት በመልአከ ብርሃን ቀሲስ አጥናፉ ማሞ የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል።

በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በመልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት በጸሎት ተፈጽሟል።

Scroll to Top