በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለ 3 ተከታታይ ዓመታት ሲያስተምራቸው የነበሩ ደቀ መዛሙርትን አስመረቀ።

የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለተከታታይ 3 ዓመታት ሲያስተምራቸው የነበሩ 22 ደቀ መዛሙርትን በዲፕሎማ እንዲሁም ለአንድ ወር ሲሰለጥኑ የነበሩ 38 ካህናትን በሰርተፊኬት በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይጨብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የኮሌጁ መሥራችና የበላይ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ የአማሮ እና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ተመራቂ ደቀ መዛሙርቱ ከምርቃት መርሐ ግብሩ በፊት በብፁዕ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል።

ሰኔ ፳፱/፳፻፲፯ ዓ/ም ኤክቱስ

©ሳሌም የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Scroll to Top