በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀትና ክብር ተከበረ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኘው በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ተከበረ።

በዕለቱም የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ ፣የመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሊቀጠበብት መሪጌታ መሠረት ይልማ፣የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አምሳሉ ሣለ ፣ለመንፈሳዊ ጉባኤ የተጋበዙ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ፣መጋቤ ሐዲስ አድነው ወንድሙ ፣ዘማሪያን፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የዲላና አካባቢው ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል።

መርሐ ግብሩ በሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል የተመራ ሲሆን የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ ያስተማሩት መጋቤ ሐዲስ አድነው ወንድሙ ሲሆኑ ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ከወጣ በኋላ በደብሩ ፍሬ ተዋህዶ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ወረብ ከቀረበ በኋላ ሁለተኛውን ትምህርት የሰጡት ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ሲሆኑ በመቀጠል ለቤተክርስቲያኑ የልማት ሥራ የማስተባበር በመጋቤ ሐዲስ አድነው ወንድሙ ተከናውኗል ።

በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ጸሎት ተደርጎ በዓሉ ፍጻሜውን አግኝቷል ።

ኤክቱስ ሐምሌ 7/2017 ዓ.ም

Scroll to Top