በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተከበረ!

ኤክቱስ ሰኔ 21/2018 ዓ.ም

በዘመነ ሐዋርያት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት ዓመታዊ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተከበረ።

ለዕለቱ የሚሆን ያሬዳዊ ዝማሬ የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ያቀረቡ ሲሆን የዕለቱን ትምህርት መጋቤ ሀዲስ ሔኖክ ፈንቴ በሚገባ አስተምረዋል።

በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች በሊቀ ልሳናት መምህር ሀብታሙ ተፈራ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተከናውኗል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ያስተላለፉ ሲሆን በንግግራቸው ዕለቱ የቤተ ክርስቲያን በዓል መሆኑንና ቤተ ክርስቲያን ማለት ደግሞ ሕንጻው ብቻ አለመሆኑን በሚገባ አስረድተዋል። በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ሰው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደመሆኑ ራሱን ካልተገቡ ልማዶችና ተግባራት እንዲጠብቅ አባታዊ መመሪያ ሰጥተው በጸሎት ፈጽመዋል።

Scroll to Top