የሀገረ ስብከቱ የንብረት የንዋየ ቅድሳትና የቅርሳ ቅርስ ክፍል ሥራና ኀላፊነት
፩.የሀገረ ስብከቱ አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በየአይነታቸው ለይቶ መዝግቦ ይይዛል ፡፡ ወጪ ሆነው ለሥራ የሚሰጡትን ዕቃዎችና ንብረቶች በህጋዊ ሰነድ ያስረክባል፣ወጪ የተደረጉ ንብረቶችን ሥራ ላይ መዋላቸውንና መጠበቃቸውን ይቆጣጠራል ፣የሚመለሱትንም መርምሮ ይረከባል፡፡
፪. ጥገና የሚያስፈልጋቸውን የሀገረ ስብከቱ ንብረቶችን በሰዓቱ እንዲጠገኑ ያደርጋል፡፡ ፫. በየዓመቱ የንብረት ቆጠራ ያደርጋል፡፡