በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ተግባራትና ኀላፊነት

፩.ስለ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የሚወጡ ደንቦችን እና መመሪያዎችን  እየተከታተለ ለየአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ያስተላልፋል አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፤

፪.የሰንበት ትምሀርት ቤት ባልተቋቋመባቸው አድባራት እና አጥቢያ አብያተክርስቲያናት  ያቋቁማል፤ይከታተላል፤

፫. በተቋቋመባቸው አድባራት እና አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤቶች በቃለ ዐዋዲው መሰረት መደራጀታቸውን፤በማእከል ደረጃ የወጣውን ስርዓተ ትምህርት መተግበራቸውን ይከታተላል ድጋፍም ያደርጋል፤

፬. ከሀገረ ስብከቱ ሌሎች ክፍላት  ጋር በመተባበር በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ተምረው የማስተማር ብቃት ያላቸውን ተተኪ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራንን ያሰለጥናል ፤

፭. በየደረጃው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እንዲቋቋም በተወሰነው መሠረት በሀገረ ስብከት እና በወረዳ ደረጃ እንዲቋቋም ያደርጋል፤ይከታተላል፤

፮.የቤተክርስቲያኒቱን ደንብና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮችን እንዲያጠኑ ያደርጋል ፤ያስደርጋል፤

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት