በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ ክፍል ሥራና ኃላፊነት

፩.የሂሳብ መዛግብትን አሟልቶ ገቢ ወጪ በህጋዊ ደረሰኝ እየሰራ በየወሩ ከወጪ ቀሪ ያለውን ያረጋግጣል በየወሩ ለጽ/ቤት መጨረሻ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

፪.የተበጀተውን በጀት ለታሰበለት ዓላማ መዋሉን ይከታተላል፡፡

፫.የሒሳብ ሰነዶችንና ቼኮችን  በጥንቃቄ በመያዝ በተፈለገ ጊዜ ለኦዲት ያቀርባል፡፡

፬.ከወረዳ እስከ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ድረስ በህጋዊ ደረሰኝ የሚሠራ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

፭. በጀት በሚደለደልበት ጊዜ ለሚደለደለው በጀት በቂ ገንዘብ መኖሩን ያረጋግጣል፡፡

፮.የበጀት ዓመቱ ከማለቁ ከሁለት ወራት በፊት የየወሩን ገቢ ገምግሞ የተከታዩን ዓመት በጀት በመሥራት ዝርዝርሩን ለአስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት