ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!!
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከአራት ወረዳ ቤተክህነት ማለትም ከመንበረ ጵጵስናና ወናጎ፣ ከይርጋጨፌ፣ከኮቸሬና ገደብ ፣ከቡሌና ረጴ ወረዳዎች ከተውጣጡ በጌዴኡፋ ቋንቋ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከሚሰጡ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር ውይይት ተደረገ።
ውይይቱ ከቤተክርስቲያን ካህናት ማሰልጠኛ ተመርቀው ወጥተው ምን አከናወኑ፣የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሲሰጡ የገጠማቸው ተግዳድሮት ነበረ፣ለገጠማቸው ችግር የወሰዱት የመፍትሔ ሃሳብ ምን ነበር፣በአገልግሎት የተገኘው ውጤት ምን ነበር፣ያሉትን ለማጽናት የጠፉትን ለመመለስ አዳዲስ ኢአማንያንን ለማምጣት ምን አከናወኑ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን።
ሰባኪያነ ወንጌሉ በአገልግሎት ላይ የገጠማቸውን ችግር ያነሱ ሲሆን መስዋዕትነት እስኪከፍሉ ድረስ ዋጋ መክፈላቸው ሰንበት ት/ቤት ማደራጀት ባዕድ አምልኮ ማጥፋት ብዙ ኢአማኒያን ማስጠመቅ ኮርስ መስጠት በማኀበራዊ ሕይወት መሳተፍ በሀዘንና በደስታ ስብከተ ወንጌል መስጠት የሚሉ የአገልግሎት ተግባራትን የዘረዘሩ ሲሆን።
በቀጣይ ከተከናወነው ያልተሰራው ስለሚበዛ በቁጭት በቋንቋ ለማስተማር ቃል ገብተዋል።
የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ በሰጡት አስተያየት ለተጠራንበት አገልግሎት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ከጠባቂነት መውጣትና በዕቅድና በዓላማ ማገልገል አገልግሎታቸው ሁሉ በውጤት የታጀበ መሆን እንዳለት በተለይ ያሉትን በማጽናትና መጠበቅ የጠፉትን ማምጣት አዳዲስ አማኒያንን ወደ ክርስትና በማምጣት ላይ አገልግሎታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በማጠቃለያው የስብከተ ወንጌል በሚገባ አገልግሎት አልተፈጸም የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በአግባቡ አውቆ ያለመፈጸም ሰባኪ ከጠባቂነት መውጣት ለዚህ አገልግሎት የተጠራን ባለዕዳዎች መሆንናችንን አንስተው የማሳመኑን የማስተማሩን ሥራ በአግባቡ መወጣት አለብን ብለዋል።
በየመንደሩ የስብከተ ወንጌል ኬላ ማቋቋምና አገልግሎትን መፈጸም በማኀበራዊ ሁነቶች ላይ መሳተፍ በቁርጠኝነት ወንጌልን ማገልገል እንደሚያስፈልግ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ፕሮጀክት የተወጋጀና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሥምሪት እንደሚሰጥ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል ።




