ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በሚከበረው በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ መንፈሳዊ ትምህርታቸው ሲከታተሉ ለነበሩ ለ44 ደቀመዛሙርት የዲቁና እንዲሁም ለ 10 ዲያቆናት የቅስና ሥልጣነ ክህነት ክህነት ሰጥተዋል።
ብፁዕነታቸው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ በንጽህናና በቅድስና ማገልገል እንዳለባቸው፣ በማይመጥናቸው ቦታ መገኘት እንደሌለባቸው እና የተቀበሉትን ትልቅ ኃላፊነት በትጋት መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክታቸውን ከአደራ ጭምር አስተላልፈዋል።




