በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ከቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጋር ተወያሀዩ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በጮርሶ ወረዳ አዲስ ለሚሰራው በቅርቡም መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ተደርጎበት ውጤታማ ሥራ ለተሰራበት የቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጋር በቀጣይ በህንጻው ሥራና ጉዳይ ላይ ከብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱም በቀጣይ በህንጻው ሥራ ላይ እስከ አሁን ከምዕመናን የተሰበሰበ ገንዘብ በማቴሪያል ቃል የተገባውን ምዕመናን ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገብተው እስከ አሁን ያላስገቡ በቀጣይ በቤተክርስቲያኑ ሕጋዊ አካውንት ማስገባት እንዳለባቸው ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል።

የህንጻ ቤተክርስቲያን ተጀምሮ ለማጠናቀቅ በቀጣይ ምዕመናን በቤተክርስቲያኑ ሕጋዊ አካውንት ገንዘብ በማስገባት ድጋፋቸውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በሌላ በአይነትም ድጋፋቸውን መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ተሰጥቶበታል።

ለቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000705214647 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማለት ቃል የገባችሁትን እንድታስገቡልን በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ስም እንጠይቃለን ።

Scroll to Top