በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለአምስት ደቀ መዛሙርት ማዕረገ ዲቁና ሰጡ!

ኤክቱስ የካቲት 16/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርታቸው ሲከታተሉ ለቆዩ ለአምስት ደቀ መዛሙርት ማዕረገ ክህነት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ለአንድ እናት ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጽመዋል።

ብፁዕነታቸው ዲያቆናቱ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ጠብቀው በትጋት ማገልገል እንዳለባቸው አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

Scroll to Top