በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕነታቸው በተገኙበት የሀገረ ስብከቱ የመማክርት ጉባኤ ከዲላው መንበረ ጵጵስና ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሄደ!!

ኤክቱስ ሰኔ 26/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የሚገኘው የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የመማክርት ጉባኤ አባላት በዛሬው ዕለት ወደ ዲላ ከተማ በመምጣት ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱም ወቅት በግንባታ ላይ የሚገኘው የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ አሁናዊ ሁኔታና የደረሰበት ደረጃ በአካል ተመልክቷል።

የመማክርት ጉባኤው ከተጠናቀቀው የመስክ ምልከታ በኋላ ከመንበረ ጵጵስና ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም ወቅት የሕንጻ ግንባታው ያለበት አጠቃላይ ደረጃና በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው አንገብጋቢ የሥራ ሂደቶች ላይ በስፋት መክረዋል።

በዚህ የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተገኝተዋል። ብፁዕነታቸው ለጉባኤውና ለኮሚቴው አስፈላጊውን አባታዊ መመሪያና ምክር የሰጡ ሲሆን የሥራ እንቅስቃሴው በተቀናጀ መልኩ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የመማክርት ጉባኤውና የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴዎች በጋራ ባደረጉት ምክክርም ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚያስችል የጋራ የሥራ ስምምነት ላይ በመድረስ ውይይታቸውን አጠናቀዋል።

Scroll to Top