በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ11-13/2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቸሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተክህነት በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ 11-13/2017 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጸሎት ሰጥተው ምስጋና ለሚገባቸው ምስጋና አቅርበው ተጠናቋል ።

በጉባኤው፦

#ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ

#መጋቤ ሠናያት መ/ር አብይ

#መጋቤ ሀዲስ ግሩም

#ዘማሪ መ/ሰ/እንግዳወርቅ በቀለ

#ዘማሪት መቅደስ መኮንን

#ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል

#የዜማ መሣሪያ ተጨዋቾች

#ከጉባኤ መጀመሪያ እስከ ፍጻሜ ድረስ የወረዳ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች የደብሩ አስተዳደሪና ካህናት እና የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ በጉባኤው ተገኝተዋል።

በጉባኤው የእግዚአብሔር ቃል የተሰበከበት ፣ልዩ ልዩ ጣዕመ ዝማሬ መንፈሳዊ ዝማሬ የቀረበበት እንዲሁም የምክረ አበው መርሐ ግብር የተከናወነበት ነው ።

Scroll to Top