በመምህር ያሬድ አደመ እና በወዳጆቹ ለዳኖ ቡልቶ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!!
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮሬ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለሚገኘው ለዳኖ ቡልቶ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በመምህር ያሬድ እና በወዳጆቹ ለአንድ ሰሞነኛ የሚሆን ሙሉ መቀደሻ አልባሳ፣ የተለያዩ መጽሐፍትና መጽሐፈ ድጓ ሳይቀር ለአብነት ተማሪዎች ጫማ የተደረገውን ድጋፍ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተረከቡ ሲሆን ድጋፉን ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው ድጋፉ ቅድስት ቤተክርስቲያን አገልግሎቷን በተሟላ መልኩ እንድትሰጥ የሚያደርግ በመሆኑ ለሌላው አርአያ መሆኑም ተገልጿል ።


