በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ።
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን የጽንሰት በዓል የይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ብዙአየሁ ዳመና የደብሩ አስተዳዳሪ ካህናትና የሐሩና የአካባቢው ምዕመናንን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ።
በዕለቱም ይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ብዙአየሁ ዳመና ለዕለቱ የሚስማማ የጌታን ዓለምን ለማዳን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር በቅዱስ ገብርኤል ብስራት መጸነሱን ዓለምን ለማዳን የተጠቀመውን የፍቅር ጥበብ በሰፊው በመግለጽ አስተምረዋል።
በመጨረሻም ለቤተክርስቲያኑ የልማት ሥራ የገቢ ማስገኛ ሥራ ምዕመናንን በማስተባበር ከተከናወነ በኋላ ጸሎትና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።



