በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

“ራሳችንን ለወንጌል አሳልፈን መስጠት ይገባናል” ሲሉ ‎ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የመንበረ ፖትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ፡፡

“ራሳችንን ለወንጌል አሳልፈን መስጠት ይገባናል” ሲሉ ‎ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የመንበረ ፖትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ፡፡

“ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በሁለተኛ ቀን የምክክር ጉባኤ ላይ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት መልእክት “‎ይህ ሁሉ ሊቃውንት እያለ ቤተክርስቲያን መቸገር የለባትም ለዚህም ራሳችንን ማዘጋጅት ይጠብቅብናል፡፡ በዘር፣ በጎሣ መከፋፈል ለቤተክርስቲያን አይጠቅማትም፣ ራሳችንን ለውንጌል አሳልፈን መስጠት ይገባናል ቀናነት እና ታዛዥነት የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ‎የመቄዶንያን የበጎ አደራጎት ማኅበር መሥራች ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ስለ ማኅበሩ አሁናዊ ሁኔታ ገልጸዉ ሁሉም ሰው የአቅሙን ርዳታ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ‎ክቡር ዶ/ር ቢኒያም በለጠ አያይዘውም እንዳሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የአየር ሰዓት በመስጠት እያገዝን ስለሆነ በድርጅታችን ስም ምስጋና እናቀርባለን ብልዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ላይ ‌‎የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከገዳማትና ከአድባራት የተወጣጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተገኝተዋል፡፡

©EOTCTV

Scroll to Top