በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ሦስተኛው ዙር ወርሃዊ የወንጌል ጉባኤ በዲላ ደ/ገ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተደረገ!!

ሦስተኛው ዙር ወርሃዊ የወንጌል ጉባኤ በዲላ ደ/ገ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተደረገ!!

ለጥምቀት በዓል መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ጥምቀትን በዲላ በሚል መጠሪያ ስም የተመሠረቱ የወጣቶች መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኀበር በብፁዕ አባታችን አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ በወር መጨረሻ እሁድ የሚደረገው የወንጌል አገልግሎት የሦስተኛ ወሩን አገልግሎት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተካሄደ።

በዕለቱ ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ መምህር ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ የትምህርትና የካህናት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ የሆኑት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ጉባኤው በሚቀጥለው ወር በመጨረሻ እሁድ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በስልክ በዚያ ለተሰበሰቡ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በአገልግሎት ምክንያት በመርሃግብሩ መገኘት እንዳልቻሉ ገልጸው ቃለ ምህዳን እና ቡራኬ ሰጥተው መርሃግብሩ በጸሎት ተፈጽሟል።

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት