በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ የንዋየ ቅድሳት እጥረት ላለባቸው የገጠር አብያተክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ።
ድጋፉ በመምህር ያሬድ አደመ በኩል የተደረገ ሲሆን ልብሰ ተክኅኖ፣ ጧፍ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ መጾርና መባረኪያ መስቀሎች፣ በርካታ የቤተ መቅደስ መጻሕፍት፣ የሥጋ ወደሙ ማክበሪያ አጎበር፣ ጸናጽል፣ ማዕፈድ የመሳሰሉ ንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደርገዋል።
ድጋፉን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተረከቡ ሲሆን ድጋፉን ላደረጉ ምዕመናን ምሥጋና አቅርበዋል።
