ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ተከናወነ!!
ለብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረስዎ መርሐግብር ተናውኗል።
በዕለቱ የሃገረ ስብከቱ የሥራ ሃላፊዎች፣ የመንበረ ጵጵስና እና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ጸሐፊ፣ የአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የካህናት ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና የምዕመናን ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል።
በዕለቱ መርሐ ግብሩ በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ የተመራ ጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የአድባራቱ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ዝማሬ ካቀረቡ በኋላ ያሬዳዊ ዝማሬ ከአድባራቱ በተውጣጡ ሊቃውንት ቀርቧል።
በመቀጠልም ከጪጩ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንና እና የበዓታ ዳግማዊት ጌቴሴማኒ ቤተክርስቲያን የመጽሐፈ ሐዲሳት መምህራን ቅኔ የቀረበ ሲሆን ከመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየት ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ቃለ ምህዳንና ቡራኬ ሰጥተው መርሐግብሩ በጸሎት ተፈጽሟል።




