በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!!

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ከሀገረ ስብከቱ ከሁሉም ወረዳ ቤተክህነት እንዲሁም አድባራት ለተወከሉ ሥራአስኪያጅና አስተዳዳሪዎች ካህናት የአስተዳደር ሠራተኞች ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ በጸሎት ተጀመረ።

ሥልጠናውን የሚሰጡት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ሲሆኑ ሥልጠናውን ሰልጣኞች በቡድን ውይይት እንዲሳተፉና የውይይቱን ውጤት ለተሳታፊ እንዲያቀርቡ በማድረግ በርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ነው።

#ሥልጠናው በኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት ዙሪያ የተሰጠ ሲሆን ልዩ ልዩ አስረጂዎችን ከቡሉይ እና ሀዲስ ኪዳን በማቅረብ የቅዱሳን አባቶችን መጽሐፍት በዋቢነት በማቅረብ አካባቢን በማየት ከሚታወቀው ነገር በመነሳት ግልጽና አሳታፊ በሆነ አቀራረብ ጥልቅ ምሥጢራትን በመግለጽና በማሳየት እየቀረበ ያለ ሥልጠና ነው።

ሁሉም ሠልጣኝ በመመልስ ፣በመጠየቅና በንቃት በመከታተል ሥልጠናውን እየተሳተፈ ይገኛል።

#የመጀመሪያው ቀን ሥልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን ነገም እንደሚቀጥል የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል።

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት