የምዕመናን አገልግሎት
የምእመናን አገልግሎት ምእመናን በሃይማኖት የጸኑ፣ በምግባር የቀኑ ይሆኑ ዘንድ በሞራል ሊገነቡ ይገባል፡፡ እንደዚህ ሲባል ግን በእውነት ላይ የተመሰረተ ምስጋና፤ ሞራላቸውን ይገነባል ለማለት እንጂ ባልሰሩት ይመስገኑ ማለት አይሆንም፡፡ የማይገባ ምስጋና ስድብ ነው፡፡ የሚገባ ምስጋና ግን ትልቅ ሽልማት ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ተጠቅሞታል፡፡ ‹‹ርቱዕ ናእኩቶ ለእግዚአብሔር በኵሉ በእንቲአክሙ አኃዊነ በከመ ይደልዎ፤ እስመ ዐብየት ሃይማኖትክሙ ወፈድፈደት ተፋቅሮትክሙ […]