በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ከተመሰረተ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት በላይ በሆነው በገርቦታ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት ተከበረ!

ኤክቱስ ኅዳር 07/2019 ዓ.ም.

ታላቁ መስተጋድል የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበትና ታላላቅ ተአምራትን ያደረገበት በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በጥንታዊውና በታሪካዊው በገርቦታ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተከብሯል።

የዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ተጠናቆ ታቦቱ ከወጣ በኋላ የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን መዝሙር አቅርበዋል።

በመቀጠል የዕለቱን ትምህርት በጌዴኡፋ ቋንቋ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በሚገባ አስተምረዋል።

በመቀጠል በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ኃይማኖት ብዙአየሁ ዳመነ የማስተባበር ሥራ አከናውነዋል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በጌዴኡፋ ቋንቋ የተለያዩ ዝማሬዎችን ካቀረቡ በኋላ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል። በንግግራቸው ሀገረ ስብከቱ በለክቻ በቋንቋ ጉባኤ አዘጋጅቶ እንደነበርና በእርሱም ብዙ ፍሬዎች እንደተገኙ ገልጸዋል። ይኸውም መርሃግብር በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ የገጠር ክፍላት እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በመጨረሻም በዓሉን ከማክበር ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትን ካህናትና ምዕመናንን አመስግነው በጸሎት ፈጽመዋል።

Scroll to Top