በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ሀገረ ስብከቱ በለክቻ በገበያ መካከል መንፈሳዊ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል!

ኤክቱስ ኅዳር 04/2019 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የክርስቶስን የመንግሥቱን ወንጌል በገጠራማ አከባቢዎች ለማድረስ ከሚሠራበት መንገድ አንዱ በገበያ መካከል እና በየአደባባዩ በአከባቢው ቋንቋ የሚደረግ ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህም በርካታ አዳዲስ አማንያንን እያገኘበት፣ የንሥሐ አባት የሌላቸውን ምዕመናን እንዲይዙ እየሠራበት ይገኛል።

ይህ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በገርቦታ 02 ቀበሌ ለክቻ ገበያ ከ4-7 የሚቆይ ሲሆም የመጀመርያው ዕለት መንፈሳዊ ጉባኤ ተከናውኗል።

Scroll to Top