በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

፳ኛው ዙር የወጣቶች መንፈሳዊ መርሃ-ግብር ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት ተካሄደ!

ኤክቱስ ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ወር በገባ በመጨረሻው ሰንበት የሚካሄደው ወርሃዊ ጉባኤ ፳ኛው ዙር መርሃ-ግብር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ተከናውኗል።

በዕለቱ መርሃ-ግብር ላይ ተጋባዥ መምህር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የአየር ማረፍያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ መምህር ቃለአብ አስተምረዋል።

ብፁዕነታቸው ለመርሃ-ግብሩ ተሳታፊዎች ቃለ-ምዕዳንና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን ከዚህ በላይ መርሃግብሩን ለማስፋት፣ ወጣቶች ራሳቸውን በመንፈሳዊ ዕውቀት ከማሳደግ ረገድ አዲስ ሊሠሩ ስለታሰቡ ቋሚ ስለሆኑ የትምህርት መርሃግብራት ተወያይተዋል። የታሰቡት መርሃግብራትም በሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ገጽ “በኤክቱስ” እንደሚገለጽ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ይህ ወርሃዊ ጉባኤ በርካታ ወጣቶችን ወደ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ለመመለስ ያለመ በመሆኑ ወጣቶቹ በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበው በጸሎት መርሃ-ግብሩን አጠናቀዋል።

Scroll to Top