በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

አሥራ ስድስት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በቡሌና ራጴ ወረዳ ቤተ ክህነት በሀሮ ወላቡ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም የሌላ እምነት አባላት የነበሩ እና የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲማሩ የቆዩ አሥራ ስድስት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

ሀገረ ስብከቱ የክርስቶስ የመንግሥቱን ወንጌል በማስፋፋት፣ ኢ-አማንያንን ወደ አሚነ ሥላሴ ለመመለስ በትጋት እየሠራ ይገኛል።

Scroll to Top