ኤክቱስ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የከምባታ ሀላባ ጠምባሮና የዳውሮ ኮንታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት የጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የሐዋርያት የአንድነት የኑሮ ማኅበር ለ4 ተከታታይ ወራት ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት በቡራዩ ከተማ አስመርቋል።
ከጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ተልከው ላለፉት 4 ወራት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ደቀ መዛሙርት ብዛታቸው 30 ሲሆን በቆይታቸውም በርካታ ትምህርቶችን እና ሥልጠናዎችን መውሰዳቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለተመራቂ ደቀ መዛሙርት አባታዊ ቡራኬና መመሪያ ሰጥተዋል።
📷 ዜና ጎርጎርዮስ
