በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

አሥራ አራት አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በገርቦታ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አሥራ አራት አዳዲስ አማንያን በዛሬው ዕለት ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

ተጠማቂያኑ በደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል አማካኝነት ከዚህ ቀደም በቱሊሴ አከባቢ በተቋቋመው የስብከተ ወንጌል ኬላ የቅድመ ጥምቀት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።

Scroll to Top