ኤክቱስ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ከሐዋርያት ሁለቱን ከነቢያት መርጦ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት የበዓለ ደብረ ታቦር ዋዜማ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል።
በዕለቱ የደብሩ መሠረተ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት ለዕለቱ የሚሆን ዝማሬ፣ ኪነ ጥበብ አቅርበዋል።
የዕለቱን ትምህርት ላዕከ ወንጌል ያሬድ አደመ “በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው” የማቴዎስ ወንጌል ፲፯፥፬ ላይ የሚገኘውን ኃይለ ቃል በማንሳት እና የዕለቱን ታሪክ በመተረክ በሰፊው አስተምረዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ጸሎት አድርገው እንዲሁም የተዘጋጀውን ችቦ ባርከው እንደ አባቶቻችን ሥርዓት የማብራት መርሃግብር ተከናውኗል።
