ኤክቱስ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
«ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው… ከድካማቸው ያረፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል።»
(ራእይ 14:13)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም በተፈጥሯዊ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለሱባኤ በቦታው በተሰበሰቡ አስራ አራት ወገኖቻችን ሕይወታቸው ማለፉንና በሰባት ወገኖቻችን ከባድና ቀላል አደጋ መፈጠሩን ስንሰማ እጅግ አዝነናል።
በዚህ አደጋ በሕይወተ ሥጋ የተለዩንን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን እግዚአብሔር አምላካችን ከጻድቃን ጉባኤ፣ ከቅዱሳን ማኅበር እንዲደምርልን እንመኛለን። በተጨማሪም ለሟች ቤተሰቦችም እግዚአብሔር አምላክ መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።
አባ ገሪማ
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
