ኤክቱስ የካቲት 16/2018 ዓ.ም
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ዓመታዊ የየካቲት ኪዳነ ምሕረት በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሯል።
ታቦቱ ከመንበሩ ከወጣ በኋላ በደብሩ ኰኵኃ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን ለዕለቱ የሚሆን ትምህርት ቀሲስ ሙሉዓለም ዐባይ የሐዋሳ ደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ አስተምረዋል።
በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ ጋባዥነት ብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በመስጠት በጸሎት ፈጽመዋል።

Pingback: lipitor medication
Pingback: ciproxine
Pingback: lasix furosemide for dogs
Pingback: dexlansoprazole generico
Pingback: vibramycin pill