በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ለሦስት ወራት መጠነኛ ዕድሳት ሲደረግለት የቆየው የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ቡራኬ ተከናወነ!

ኤክቱስ የካቲት 08/2018 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ወራት ያኽል መጠነኛ ዕድሳት ሲደረግለት ቆይቶ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡራኬ ተከናውኗል።

በዕለቱ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምሕረት፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና ዲያቆናት ተገኝተዋል።

Scroll to Top