ኤክቱስ የካቲት 2/2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪና የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በቆይታቸውም ስለ ሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ዳራና አሁናዊ የልማት እንቅስቃሴ ዝርዝር ገለጻ አቅርበውላቸዋል።
ብፁዕነታቸው በገለጻቸው ወቅት የሀገረ ስብከቱ ትኩረትና ፍላጎት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወደተሻለ ደረጃ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም መሠረት ቤተክርስቲያኗ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ እንደምትገኝ አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ በእነዚህ የልማት ሥራዎች ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችንና የግብዓት እጥረቶችን ለክቡር ሚኒስትሩ አቅርበዋል።
